ስፓርት

የታዳጊዎች የፓይለት ፕሮጀክቶችን ፍሬ የምናይበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም -አቶ ኢሳያስ ጅራ

By Feven Bishaw

April 18, 2022

አዲስ አበባ፣ሚያዚያ 10፣2014 (ኤፍ ቢሲ) በየክልሉ የሚገኙ የታዳጊዎች የፓይለት ፕሮጀክቶችን ፍሬ የምናይበት ጊዜ ሩቅ አይደለም ሲሉ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚደንት አቶ ኢሳያስ ጅራ ተናገሩ፡፡

ፕሬዚደንቱ ከሰሞኑ በተለያዩ ክልሎች የሚካሄዱትን የታዳጊዎች እግር ኳስ ፓይለት ፕሮጅክቶች ከጎበኙ በኋላ ከፌዴሬሽኑ የዝግጅት ክፍል ጋር ቆይታ ባደረጉት ቆይታ ስልጉብኝታቸው ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡