አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የበቆሎ ማሳውን ለመታደግ የሞከረ ግለሰብ በዝሆን ጥቃት ህይወቱ ማለፉ ተሰምቷል፡፡
ዝሆኑ ጉዳት ያደረሰው በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በኮንታ ዞን ነው፡፡
የኮንታ ዞን ፖሊስ አዛዥ ምክትል ኢንስፔክተር ባሳ በየነ እንደገለፁት ፥ በኮንታ ዞን አመያ ዙሪያ ወረዳ ሴሬ ቀበሌ ትናንት ምሽት 4:00 ሰዓት ሟች የበቆሎ ማሳውን ከዝሆን ለመጠበቅ ሲሞክር ነው በድርጊቱ በተቆጣው ዝሆን ጥቃት ህይዎቱ ያለፈው ።
ጥቃት አድራሹ ዝሆን አርሶ አደሩን በኩምቢው በመያዝ በእግሮቹ በመርገጡ ህይወቱ ሊያልፍ ችሏል፡፡
ከዚህ ቀደም በአካባቢው ጎሽ ተመሳሳይ ጥቃት አድርሶ እንደነበር ያስታወሱት ዋና አዛዡ ፥ ህብረተሰቡም እራሱን ከመሰል አደጋ እንዲጠብቅ መልዕክት ማስተላለፋቸውን ደቡብ ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ድርጅት ዘግቧል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!