አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በመዲናዋ እየተስተዋለ ያለውን የኑሮ ውድነት ለመግታት የኅብረት ሥራ ማኅበራት ከሌብነትና ብልሹ አሰራር መጽዳት እንዳለባቸው የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ገለጸ፡፡
የምርት አቅርቦትንና ሥርጭትን ከፍ በማድረግ የኑሮ ውድነትን ለመግታት ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየሰራ መሆኑን ንግድ ቢሮው ገለጿል።
የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ ሃላፊ አቶ አደም ኑሪ ÷ የንግድና ኅብረት ሥራ ማኅበራት በዘጠኝ ወራት ውስጥ ያከናወናቸውን ሥራዎች ከባለድርሻ አካላት ጋር መገምገሙንም ተናግዋል፡፡
የንግድ አሰራርን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በማጠናከርና የተጀመሩ የገበያ ማዕከላት በወቅቱ ተጠናቀው ሥራ ላይ እንዲውሉ በማድረግም በዘርፉ የሚታየውን የሙስና እና ብልሹ አሰራር ለመግታት ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራ በውይይት መድረኩ ተነስቷል፡፡
የኅብረተሰቡን ፍላጎት ማዕከል ያደረገ የድጎማና የግብርና ምርቶች እቅርቦት እንዲሁም የገበያ ትሥሥሩን ከፍ በማድረግ እየተስተዋለ ያለውን የኑሮ ውድነት ለመግታት ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሠራ መሆኑም ነው የተመለከተው፡፡
የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ÷ በዘጠኝ ወራት ውስጥ በድጎማ ምርቶች አቅርቦትና ስርጭት፣ የእሁድ ገበያ የምርት አቅርቦትና ተደራሽነት፣ መደበኛ ያልሆኑ የንግድ እንቅስቃሴዎችን ሥርዓት ለማስያዝ የተሰሩ ስራዎችንና በተዛማጅ ነጥቦች ላይ ዝርዝር ሪፖርት ቀርቦ እንደተወያየበትም ነው ከቢሮው ያገኘነው መረጃ የሚያመለክተው፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!