የሀገር ውስጥ ዜና

ኮሚሽኑ ለአገራዊ ምክክሩ ህገ ደንቦችን፣ መመሪያዎችን እና ፖሊሲዎችን እያዘጋጀ መሆኑን ገለጸ

By Meseret Awoke

April 20, 2022

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን ህገ ደንቦችን፣ መመሪያዎችን፣ ፖሊሲ እና ስትራቴጂዎችን እያዘጋጀ መሆኑን አስታውቋል፡፡

የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ባደረጉት ቆይታ÷ ኮሚሽኑ በእስካሁኑ ሂደት ከተቋማት ጋር ውይይት በማድርግ ልምድ እና ተሞክሮ መውሰዱን ተናግረዋል።

በቀጣይም ከመገናኛ ብዙሃን ፣ ከፖለቲካ ፓርቲዎች እና ከሌሎች ተቋሟት ጋር እንደሚወያዩ ነው ዋና ኮሚሽነሩ ያስታወቁት፡፡

“ አጀንዳ የሚቀርጸው ህዝቡ ነው፤ ውሳኔውም የህዝብ ነው” የሚሉት ዋና ኮሚሽነሩ፥ ምሁራንም የህዝብን አጀንዳ በማቅረብ ይሳተፋሉ ብለዋል፡፡

ኮሚሽኑ ለውይይቱ ቅድመ ዝግጅት ከማድረግ ባለፈ የተለያዩ ተግባራትን በወራት እና በዓመታት ለመስራት የወሰነ ሲሆን÷ አጀንዳ የማሰባበብ ስራው በቅረቡ ይጀመራል ነው ያሉት፡፡

ለውጤታማነቱ ሁሉም ህብረተሰብ በንቃት ሊሳተፍ እንደሚገባ ዋና ኮሚሽነሩ ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በአልማዝ መኮንን

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!