የሀገር ውስጥ ዜና

የክልል መንግስታት ለዐድዋ ድል በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል

By Tibebu Kebede

March 01, 2020

አዲስ አበባ፣ የካቲት 22፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የክልል መንግስታት፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር እና የፌደራል ተቋማት ለዐድዋ ድል መታሳቢያ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት እያስተላለፉ ነው።

የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ባወጣው መግለጫ፥ የአድዋ ድል የሁሉም የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ድል ነው ብሏል።