የሀገር ውስጥ ዜና

ዶክተር ፍጹም አሰፋ ከጃፓን ልማት የትብብር ኤጀንሲ ልኡክ ጋር ተወያዩ

By Feven Bishaw

April 26, 2022

 

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የፕላን እና ልማት ሚኒስትር ዶክተር ፍጹም አሰፋ ከጃፓን ልማት የትብብር ኤጀንሲ (ጃይካ) ልኡክ ጋር ተወያይተዋል፡፡

ዶክተር ፍጹም በፕሮፌሰር ኬኒቺ ኦህኖ ከተመራው የኤጀንሲው ልኡክ ጋር የአስር ዓመት የልማት ዕቅድ አተገባበር እንዲሁም ያለበት ደረጃ፣ ውጤት እና ያጋጠሙ ችግሮች ላይ መክረዋል፡፡