የሀገር ውስጥ ዜና

ከሳዑዲ 1 ሺህ 29 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

By Meseret Awoke

May 04, 2022

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በዛሬው ዕለት በሶስት ዙር በተከናወነ ዜጎችን ከሳኡዲ አረቢያ የመመለስ ስራ በአጠቃላይ ቁጥራቸው 1 ሺህ 29 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ፡፡

ወደ ሀገራቸው ከተመለሱ ዜጎች ውስጥ አምስት ህጻናትና 1 ሺህ 24 ወንዶች መሆናቸውን ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ለተመላሽ ዜጎችም ተገቢውን ድጋፍ እና ክብካቤ በማድረግ ወደ ተዘጋጀላቸው የማቆያ ማእከላት እንዲሄዱ መደረጉም ነው የተገለጸው፡፡

እስካሁን በተከናወነው ዜጎችን የመመለስ ስራ ቁጥራቸው ከ18 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያንን መመለስ ተችሏል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን፡፡