የሀገር ውስጥ ዜና

በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትሯ የተመራ ቡድን በሶማሌ ያለውን የድርቅ ሁኔታ ለመመልከት ጎዴ ገባ

By Amare Asrat

May 05, 2022

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ የተመራ ቡድን በሶማሌ ክልል ያለውን የድርቅ ሁኔታ ለመመልከት ጎዴ ገብቷል፡፡

ቡድኑ በሸበሌ ዞን በሚኖረው ቆይታ÷ በድርቅ ምክንያት ከብቶቻቸውን ያጡ አርብቶ አደር ቤተሰቦች እስካሁን እየተደረገላቸው ያለውን የእርዳታና ድጋፍ ሁኔታ እንደሚመለከት ተገልጿል።

አርብቶ አደሮቹን በዘላቂነት ማቋቋም በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ከክልሉ የስራ ኃላፊዎች ጋር ቡድኑ እንደሚወያይ ኢዜአ ዘግቧል፡፡