አዲስ አበባ ፣ የካቲት 24 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ)በማሊ በደረሰ ጥቃት የ6 ሰወች ህይወት ማለፉ ተነገረ፡፡
በማሊ በሞንዶሮ ከተማ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት ስድስት ወታደሮች ሲገደሉ 10 ሰዎች ደግሞ ቆስለዋል ፡፡
በአጸፋውም የሃገሪቱ ወታደራዊ ሃይል ባደረሰው የአየር ጥቃት በታጣቂዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሲደርስ ፤ የታጣዊቆቹ በርካታ ተሽከርካሪዎች መውደማቸው ነው የተገለፀው።
ከአልቃይዳ ጋር ግንኙነት እንዳላቸው የሚነገረው ታጣቂዎች በመስከረም ወር በወታደራዊ ካምፕ እና በቦልኪሴይ ባደረሱት ጥቃት 40 ወታደሮች መገደላቸው የሚታወስ ነው ፡፡
በሀገሪቱ እየተባባሰ የመጣውን ዓመፅ ለማስቆም የማሊው ፕሬዚዳንት ኢብራሂም ቡባካር ኬታ ከጅሃዶች ጋር መደራደር እንደሚፈልጉ ገልፀዋል ፡፡
ምንጭ÷ቢቢሲ