የሀገር ውስጥ ዜና

በደቡብ ክልል በሦስት ዓመታት 40 ሚሊየን የፍራፍሬ ችግኝ ለመትከል ታቅዷል

By Feven Bishaw

May 06, 2022

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ክልል የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እየተደረገ ባለው ጥረት በሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት እስከ 40 ሚሊየን የፍራፍሬ ችግኝ ለመትከል ታቅዶ እየተሰራ መሆኑ ተመለከተ ።

የደቡብ ክልል የ30-40-30 የፍራፍሬ ልማት መንደር ፕሮጀክት ማስጀመሪያ ስነ ስርአት በሀዲያ ዞን ሻሾጎ ወረዳ ቦኖሾ ጎልቾ ቀበሌ ተካሂዷል።