የሀገር ውስጥ ዜና

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ሰላምና ፀጥታን ለማስከበር ለሰሩ የፀጥታ አካላት በተዘጋጀው የእውቅና መርሐ ግብር ለመታደም አሶሳ ገቡ

By Melaku Gedif

May 26, 2022

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዲሪ መከላከያ ሰራዊት ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ሰላምና ፀጥታን ለማስከበር ለሰሩ የፀጥታ አካላት በተዘጋጀው የእውቅና መርሐ ግብር ለመታደም አሶሳ ከተማ ገቡ፡፡

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ወደ ከተማዋ ሲገቡ የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ አሻድሊ ሀሰንን ጨምሮ የካቢኒ አባላት አቀባበል አድርገውላቸዋል።

በመርሐ ግብሩ ለመከላከያ ሰራዊትና ለሌሎች የፀጥታ ሀይሎችና ተቋማት እውቅና እንደሚሰጥ ይጠበቃል። በአፈወርቅ እያዩ