የሀገር ውስጥ ዜና

የጃፓን መንግስት ለከተሞች የደረቅ ቆሻሻ አወጋገድ ድጋፍ ሊያደርግ ነው

By Tibebu Kebede

March 05, 2020

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 26 ፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በጃፓን ፉኮካ ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር ከሆኑት ማጹፉጂ ኮጂ ጋር ተወያይተዋል።

በዚህ ወቅትም ዩኒቨርሲቲው ከኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በመተባበር በአዲስ አበባ እና በባህርዳር ከተሞች ከደረቅ ቆሻሻ አወጋገድ ጋር በተያያዘ በሚያከናውናቸው ተግባራት ዙሪያ መክረዋል።