ስፓርት

ዋልያዎቹ ከሌሴቶ አቻቸው ጋር በአቻ ውጤት ተለያይተዋል

By Feven Bishaw

May 28, 2022

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከሌሴቶ አቻው ጋር ባደረገው የአቋም መለኪያ ጨዋታ አንድ አቻ ተለያይቷል፡፡

በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ሌሴቶ በ20ኛው ደቂቃ በማክሀ ቱሜሎ አማካኝነት የመጀመሪያውን ግብ አስቆጥራለች፡፡