የሀገር ውስጥ ዜና

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተመራ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ለሥራ ጉብኝት ባሌ ሮቤ ገባ

By Shambel Mihret

June 02, 2022

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተመራ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ለሥራ ጉብኝት ባሌ ሮቤ ገብቷል፡፡ በጉብኝቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ የፌደራል እና የክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ የቀድሞ ጠቅላይ ሚስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ፣ የዓለም ባንክ የኢትዮጵያ ተወካይ ኡስማን ዲዮን እና ሌሎችም ተሳታፊ መሆናቸውን ኢቢሲ ዘግቧል። የልዑካን ቡድኑ በባሌ ዞን እየተከናወኑ ያሉ የግብርና ሥራዎችን ተዘዋውሮ ይመለከታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-