አዲስ አበባ፣ ግንቦት 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ለአብረሆት ቤተ መጻሕፍት 7 ሺህ መጽሃፍ ማበርከቱን የጉባኤው ጠቅላይ ፀሐፊ ሊቀ ትጉኃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ ተናግረዋል፡፡
መጽሃፍቱን ከጉባኤው ጽህፈት ቤትና ከአባል ቤተ እምነቶቹ በማስተባበር ዛሬ ለቤተ መጻሕፍቱ ማስረከብ መቻሉን ነው የገለጹት፡፡
በርክክብ መርሐ ግብሩ ላይ የጉባኤው የሥራ አስፈፃሚ ቦርድ አባላት፣ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስተባባሪ ኮሚቴ፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አስተባባሪ ኮሚቴ እና የደራሲያን ማህበር አባላት መገኘታቸውን የተቋሙ መረጃ ያመላክታል።