የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮጵያ እና እስራኤል በንግድና ኢንቨስትመንት ዘርፍ በጋራ ለመስራት ስምምነት ተፈራረሙ

By Shambel Mihret

June 03, 2022

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ እና የእስራኤል  ንግድ  ምክር ቤት በንግድና ኢንቨስትመንት ዘርፍ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

ስምምነቱ  በግብርና፣ በኢንዱስትሪ  እና  በግል  ሴክተሮች   ዘርፍ አብሮ  ለመስራት  የሚያስችል ሲሆን÷ የሁለቱን አገራት የንግድና ኢንቨስትመንት ዘርፍ ለማሳደግ የምክክር መድረክ በአዲስ አበባ ተካሂዷል።

በመድረኩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴንን ጨምሮ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል፣ ሌሎች ከፍተኛ የፌደራልና የክልል የስራ ኃላፊዎች፣ የንግድና የዘርፍ ማህበራት አመራሮች፣ በኢትጵያ የእስራኤል አምባሳደር አለልኝ አድማሱ እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።

መድረኩ የሁለቱን አገራት የቆየ ጥብቅ ዲፕሎማሲያዊ፣ ምጣኔ ኃብታዊ፣ ኃይማኖታዊ እና ባህላዊ ግንኙነት ያጠናክራልም ተብሏል።

በቀጣይም እስራኤል ያላትን የቴክኖሎጂ ልህቀት ተጠቅማ በኢትዮጵያ ያለውን ጸጋ በማልማት የሁለቱን አገራት ህዝቦች ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ ምክክሩ እገዛ እንደሚያደርግ ተገልጿል።

በዱሬቲ ቶለሳ