የሀገር ውስጥ ዜና

የፖሊስ አመራርና አባላት የምስጋናና የእውቅና አሰጣጥ መርሃ ግብር እየተካሄደ ነው

By Feven Bishaw

June 05, 2022

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የፖሊስ አመራርና አባላት የምስጋናና የእውቅና አሰጣጥ መርሃ ግብር በመስቀል አደባባይ እየተካሄደ ነው፡፡

በህግ ማስከበር ፣ በህልውና እና በህብረ ብሄራዊ አንድነት ዘመቻዎች ወቅት ጀግንነት ለፈፀሙና የላቀ የስራ ውጤት ላስመዘገቡ የፖሊስ አመራርና አባላት ነው የምስጋናና የእውቅና አሰጣጥ መርሃ ግብሩ “በመስዋዕትነታችን የሀገራችን አንድነትና የህዝባችን ሰላም ይረጋገጣል” በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ የሚገኘው፡፡

 

በአዳነች አበበ እና በለሊሴ ተስፋዬ