የሀገር ውስጥ ዜና

ዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ በሶማሌ ክልል ለ1 ሺህ አባወራዎች ድጋፍ አደረገ

By Feven Bishaw

June 06, 2022

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ባለፈው ሳምንት በሶማሌ ክልል ቱሊጉሌድ ወረዳ ለ1 ሺህ አባወራዎች ድጋፍ አድርጓል፡፡

ድጋፉ የበቆሎንና የማሽላ ዘርን የሚያካትት ሲሆን÷ በክልሉ ላሉ 4 ሺህ አባወራዎችም የስንዴ ስርጭት በመካሄድ ላይ እንደሚገኝ ከኮሚቴው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡