የሀገር ውስጥ ዜና

ወ/ሮ መሠረት ዳምጤ የፌደራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ዋና ኦዲተር ሆነው ተሾሙ

By Meseret Awoke

June 09, 2022

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 2 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 6ዙር 1ኛ ዓመት 12ኛ መደበኛ ጉባዔ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የቀረቡለትን የፌደራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ዋና ኦዲተር እና ምክትል ዋና ኦዲተር ሹመት በሙሉ ድምፅ አጽድቋል።

በዚህም ወይዘሮ መሠረት ዳምጤ ጫንያለው የፌደራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ዋና ኦዲተር እንዲሁም አቶ አበራ ታደሰ ኢትቻ ደግሞ ምክትል ዋና ኦዲተር ሆነው ተሾመዋል።

ተሿሚዎቹ በምክር ቤቱ አባላት ፊት ቀርበው ቃለ መሃላ መፈፀማቸውን ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!