አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮ ኢንጅነሪንግ ግሩፕ የአዳማ የግብርና ማምረቻ ኢንዱስትሪ ባለፉት 6 ወራት ከ516 ነጥብ 9 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ የግብርና ማሽነሪዎችን በመገጣጠም ወደ ኢኮኖሚው እያስገባ መሆኑ ተገለፀ።
ከእነዚህ ውስጥ በ2014 ዓ.ም ከ277 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር በላይ ለበልግና ለመኸር እርሻ አገልግሎት የሚሆኑ የተለያዩ የፈረስ ጉልበት ያላቸው ትራክተሮች ፣ የትራክተር ተቀፅላ መሳሪያዎች እንዲሁም የተለያዩ የውሃ ፓምፖችን በመገጣጠም በመላ ሀገሪቱ ግዥለመፈፀም ጥያቄ ላቀረቡ አካላት ማስረከብ መቻሉን የኢትዮ ኢንጅነሪንግ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አምባሳደር ምስጋናው አረጋ ተናግረዋል ።