የሀገር ውስጥ ዜና

በ22ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና የተሳተፈው ልዑክ አቀባበል ተደረገለት

By Shambel Mihret

June 15, 2022

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሞሪሺየስ በተካሄደው 22ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና የተሳተፈው ልዑክ አቀባበል ተደረገለት።

ኢትዮጵያ 22ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮናን በ4 ወርቅ፣ 6 ብር እና 4 ነሐስ በድምሩ 14 ሜዳሊያ በመሰብሰብ 5ኛ ደረጃ ይዛ አጠናቃለች።

በዚህ ሻምፒዮና የተካፈለው ልዑክ አዲስ አበባ ሲደርስ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር መስፍን ቸርነትን ጨምሮ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ስራ አስፈፃሚ አባላት በተገኙበት አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ቡድኑ በአዲስ አበባ አራራት ሆቴል የማበረታቻ የገንዘብ ሽልማት እንደሚሰጠው  ኢዜአ ዘግቧል፡፡