የሀገር ውስጥ ዜና

ሚኒስቴሩ በአማራ እና አፋር ክልሎች በጦርነቱ የአካል ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ድጋፍ አደረገ

By Mikias Ayele

June 15, 2022

አዲስ አበባ፣ሰኔ 8፣2014 (ኤፍ ቢሲ) የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በአማራ እና አፋር ክልሎች በጦርነቱ የአካል ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው የዊልቸር እና የክራንች ድጋፍ አድርጓል።

የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ÷ በአማራ ክልል የተጠናከረ የሥነ ልቦና ድጋፍ ጭምር እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

የአማራ ክልል ሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኀላፊ ወይዘሮ አስናቁ ድረስ  በበኩላቸው÷ በአማራ ክልል ጦርነቱ በሴቶች እና ሕጻናት  ላይ ያደረሰው ጉዳት  የከፋ እንደሆነ አስረድተዋል፡፡

ተባብረን ከሠራን ከችግር መውጣት እንችላለን  ያሉት ሀላፊዋ  ሁሉም የሚችለውን ድጋፍ እንዲያደርግ  ጥሪ አቅርበዋል።

በኢትዮጵያ በተከሰቱ ሰው ሰራሽ እና የተፈጥሮ አደጋዎች ጉዳት የደረሰባቸው ዜጎችን በዘላቂነት ለመደገፍ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ከአጋር አካላት ጋር ጥረት እያደረገ መሆኑን አሚኮ ዘግቧል፡፡