የሀገር ውስጥ ዜና

ኢ/ር ታከለ በቀጣይ ክረምት ለሚደረገው የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር እየተከናወነ ያለውን የቅድመ ዝግጅት ስራ ጎበኙ

By Tibebu Kebede

March 07, 2020

የአዲስ አበባ ፣ የካቲት 28 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በቀጣይ ክረምት ለሚደረገው የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር እየተከናወነ ያለውን የቅድመ ዝግጅት ስራ ጎብኝተዋል።

በቀጣዩ ክረምት ለሚደረገው የ10 ሚሊየን ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በዘጠኝ የችግኝ ማፍያ ጣቢያዎች አራት ሚሊየን የተለያዩ ሀገር በቀል የዛፍ ችግኞችን ለማዘጋጀት እየተሰራ መሆኑ ተገልጿል።