የሀገር ውስጥ ዜና

1 ሺህ 34 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

By Meseret Awoke

June 20, 2022

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 13 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶስት ዙር በተከናወነ ዜጎችን ከሳዑዲ አረቢያ የመመለስ ስራ 1 ሺህ 34 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።

ከእነዚህ ውስጥ አንድ ህጻን መሆኑን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።

ለተመላሽ ዜጎችም ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ወደ ተዘጋጀላቸው የማቆያ ማእከላት እንዲሄዱ ተደርጓል፡፡

እስካሁን ድረስ በተከናወነው ዜጎችን የመመለስ ስራ 39 ሺህ 887 ኢትዮጵያውያንን መመለስ ተችሏል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!