የሀገር ውስጥ ዜና

በአረብ ኤምሬቶች የኮሮናቫይረስ የተገኘባቸው ሁለቱ ኢትዮጵያውን ለሁለት ዓመታት በዚያው የኖሩና በቅርቡ ጉዞ ያላደረጉ ናቸው ተባለ

By Meseret Demissu

March 08, 2020

አዲስ አበባ፣ የካቲት 29፣ 2012(ኤፍ.ቢ.ሲ ) ሰሞኑን በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሁለት ኢትዮጵያውን በሀገሪቱ ለሁለት ዓመታት የኖሩ እና በቅርብ ጊዜ ውስጥ ወደ ኢትዮጵያ ያረጉት ምንም ዓይነት የጉዞ ታሪክ እንደሌላቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

ከሰሞኑ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች 13 ሰዎች በሀገሪቱ የኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው እና ከእነዚህ ውስጥም ሁለቱ ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን አስታውቆ ነበር የኢፌዴሪ የጤና ሚኒስቴር ይህንንም ተከትሎ ሁለቱ ኢትጵያውያን ወደ ሀገራቸው የቅርብ ጊዜ የጉዞ ታሪክ እንዳላቸው ከሀገሪቱ የጤና ሚኒስቴር መረጃዎችን ሲያሰብባስብ ነበር።