ዓለምአቀፋዊ ዜና

የቡድን 7 አባል ሀገራት በአየር ንብረት ለውጥ ላይ የሚመክር የመወያያ ክበብ ለመመስረት ተስማሙ

By Alemayehu Geremew

June 28, 2022

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቡድን 7 አባል ሀገራት መሪዎች የዓለም ሙቀት መጨመርን ለመግታት የሚመክር የመወያያ ክበብ ለመመስረት ተስማምተዋል፡፡

ክበቡ ፈቃደኛ የሆኑ ሀገራትን በማስተባበር የዓለም ሙቀት መጨመርን መቋቋም በሚቻልበት ሁኔታ ላይ እንደሚሰራ በመግለጫቸው አስታውቀዋል፡፡

የፓሪሱን የዓየር ንብረት ለውጥ ስምምነት ለመተግበር ቁርጠኛ የሆኑ ሀገራትን በአባልነት ለማቀፍ ክበቡ ክፍት መሆኑም ነው የተነገረው፡፡

በተለይ ክበቡ ከኢንዱስትሪው ዘርፍ ለሚመነጭ በካይ ጋዝ ልዩ ትኩረት እንደሚሰጥና ሀገራትና ኢንዱስትሪዎቻቸው ለዓለም አቀፉ ህግ እንዲገዙ እንደሚሰራ የቡድን 7 አባል ሀገራት መሪዎች የሦስት ቀናት ጉባዔያቸውን ሲያጠናቅቁ በሰጡት መግለጫ ማስታወቃቸውን ሲ ጂ ቲ ኤን ዘግቧል፡፡