የሀገር ውስጥ ዜና

ከትግራይ ልዩ ኃይል የመጡ የሽብር ቡድኑ አባላት በቁጥጥር ሥር ዋሉ

By Meseret Awoke

July 02, 2022

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 25 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከትግራይ ልዩ ኃይል የመጡ የሽብር ቡድኑ አባላት በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ።

የሽብር ቡድኑ ሁለት አባላት አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ቱሉ ዲምቱ አካባቢ 11:00 ሰዓት ላይ በቁጥጥር ሥር እንዲውሉ መደረጉንም ነው አስተዳደሩ ያስታወቀው።

በቁጥጥር ሥር የዋሉት ዘመን ገ/እግዚአብሔር (የጥበቃ መምሪያ አባል የነበረ የፈንጂ ባለሙያ) እንዲሁም ገ/ኪዳን ገ/ጻድቅ የልዩ ኃይሉ አባል መሆናቸውን ገልጿል።

አሁን ላይም በሽብር ቡድኑ አባላት ላይ ከፌደራል ፖሊስ ጋር በመሆን ምርመራ መጀመሩንም አስታውቋል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!