አዲስ አበባ፣ ሰኔ 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሁሉም ከተሞች 196 ነጥብ 8 ሚሊየን ችግኞች እንደሚተከሉ የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒ ገለጹ፡፡
በ4ኛው ዙር የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር “ዐሻራችን ለከተሞቻችን” በሚል መሪ ቃል ሚኒስቴሩ ከለገጣፎ ለገዳዲ ከተማ አስተዳደር ጋር በመተባበር የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር አካሂዷል።
ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒ በመርሐ ግብሩ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ ኢትዮጵያ ለፈተናዎቿ እጅ ሳትሰጥ ወደፊት ለመጓዝ አበክራ እየሠራች ነው ብለዋል።
የአየር ንብረት ለውጥ የዓለም ፈተና ሆኖ መቀጠሉን አስታውሰው÷ ችግሩን ለመቅረፍ ኢትዮጵያ ድንበር ተሻጋሪና ተሞክሮ የሚሆን ሥራ እያከናወነች መሆኑንም አስገንዝበዋል፡፡
አክለውም በከተሞች 196 ነጥብ 8 ሚሊየን ችግኞች ይተከላሉ ብለዋል፡፡
በመርሐ ግብሩ ላይ ÷ የከተማና መሰረት ልማት ሚኒስትር ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒን ጨምሮ የጋምቤላ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ካንክዌ ጃክ እንዲሁም ከሁሉም የሀገሪቱ ከተሞች የመጡ ከንቲባዎችና የለገጣፎ ለገዳዲ ከተማ አስተዳደር ነዋሪዎች መሳተፋቸውን ኦቢኤን ዘግቧል፡፡
ለተጨማሪ መረጃ