አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አየርላንድ በኢትዮጵያ ለሰብዓዊ እርዳታ የሚውል ተጨማሪ ሁለት ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ አደረገች፡፡
አየርላንድ ያደረገችው ድጋፍ በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች በግጭት እና ድርቅ ሳቢያ ችግር ውስጥ ለሚገኙ እና አስቸኳይ የሰብዓዊ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች የሚውል መሆኑ ተገልጿል፡፡
በዓለም አቀፍ የነፍስ አድን ኮሚቴ በኩል የሚሰራጨው ይህ ድጋፍ÷ በኢትዮጵያ የሚደረገውን የሰብአዊ እርዳታ ምላሸ ለማሳደግ እንደሚያስችል በኢትዮጵያ ከአየርላንድ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!