አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ከሕዝብ በተነሱ ጥያቄዎች ላይ እና መፍትሄዎቻቸው ዙሪያ ዛሬ ከአስፈፃሚ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ጋር እየመከሩ ነው።
ሕዝቡ ያነሳቸው የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ምላሽ እንዲያገኙ የምክር ቤት አባላቱ በቁርጠኝነት እንደሚሠሩም አረጋግጠዋል፡፡
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በየካቲት ወር 2014 ዓ.ም በምርጫ ክልላቸው በመገኘት ከመረጣቸው ሕዝብ ጋር ውይይት ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡
በወቅቱም ዘርፈ ብዙ ጥያቄዎች ተነስተው እንደነበር ተጠቅሷል፡፡
በተወያዩበት ወቅት ከሕዝቡ በተነሱ ጥያቄዎች ላይ ዛሬ ከአስፈፃሚ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ጋር በተነሱ ጥያቄዎችና መፍቴዎቻቸው ዙሪያ እየመከሩ መሆኑን ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰ