የሀገር ውስጥ ዜና

በአለም አቀፍ የጦር መሳሪያ አዘዋዋሪ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ በሽፋን እንዲገባ የተደረገ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የጦር መሳሪያ በቁጥጥር ስር ዋለ

By Tibebu Kebede

March 10, 2020

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 1፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አለም አቀፍ የጦር መሳሪያ አዘዋዋሪ ቡድን በጅቡቲ ወደብ በኩል ወደ ኢትዮጵያ በሽፋን ያስገባው ሁለት ኮንቴነር ህገወጥ የጦር መሳሪያ በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ማድረጉን የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡

መነሻውን ከቱርክ ሜርሲን ወደብ ያደረገው ህገወጥ የጦር መሳሪያው፤ በጅቡቲ ወደብ በኩል ወደ ኢትዮጵያ በሽፋን ገብቶ በቁጥጥር ስር የዋለው፤ በወደቡ ለአምስት ወራት ያህል በድብቅ ተቀመጦ፤ በረቀቀ መንገድ ወደ ሀገር ውስጥ ከገበ በኋላ መሆኑን አገልግሎት መስሪያ ቤቱ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ አመልክቷል፡፡