አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) “እንደ ሀገር የገጠመንን ሰው ሰራሽ እና ተፈጥሮአዊ ተግዳሮቶችን መሻገር የምንችለው ከምንም በላይ ማህበራዊና ተፈጥሯዊ እሴቶቻችንን ስንከባከብና ስናጠናክር ነው” ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አቶ ታገሰ ጫፎ ተናገሩ።
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት እና የምክር ቤቱ ሠራተኞች “ዐሻራችን ለትውልዳችን፤ ለትውልድ እንስራ፤ ለኢትዮጵያ እንትከል” በሚል መሪ ሐሳብ 4ኛውን የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር በአዲስ አበባ አካሂደዋል፡፡
በመርሐ ግብሩ ላይ ከ2 ሺህ በላይ የተለያዩ ችግኞች ተተክለዋል፡፡
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ፥ የምክር ቤት አባላት ወደተመረጡበት አካባቢ ሲመለሱ ለአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ውጤታማነት የበኩላቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡
“ተፈጥሮን ስንከባከብ መልሳ ትንከባከበናለች” ያሉት አፈ ጉባዔው፥ ህብረተሰቡ ከተፈጥሮ ጋር መጣላት እንደሌለበትና ለአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ትኩረት ሰጥቶ ሊሠራ ይገባል ማለታቸውን ኦ ቢ ኤን ዘግቧል፡፡
በርካታ የዓለም ሀገራት ተፈጥሮን ባለመንከባከባቸው ድርቅና ጎርፍን ጨምሮ ለተለያዩ ተፈጥሮአዊ አደጋዎች መጋለጣቸውን ገልጸው፥ “እንደ ሀገር ተመሳሳይ ችግር እንዳይገጥመን ተፈጥሮን ልንከባከብ ይግባል” ነው ያሉት።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!