አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ኢራን የቀጠናው ስጋት በማትሆንበት እና ተፅዕኖዋን መግታት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ከባህረ ሰላጤ ሀገራት ጋር ዛሬ ይመክራሉ፡፡
ፕሬዚዳንቱ የአራት ቀናት የአካባቢው አገራት ጉዞ ማሳረጊያ ባደረጉት በዚህ ጉባኤ የባህረ ሰላጤው ሀገራት በኢራን ጉዳይ ትብብራቸው በሚጠናከርበትና የአሜሪካን አቋም ያሳያል ያሉትን የመካከለኛው ምስራቅ እቅዳቸውንም ይፋ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በቀይ ባህሯ የወደብ ከተማ ጅዳ ከስድስት የአረብ ባህረ ሰላጤ ሀገራትን ጨምሮ ከግብፅ፣ ዮርዳኖስና እና ኢራቅ መሪዎች ጋር ነው የሚመክሩት።
ከባህረ ሰላጤው የትብብር ምክር ቤት ስብሰባ ቀደም ብሎ ዋይት ሀውስ የሩሲያ ባለስልጣናት ባለፉት ሳምንታት ሁለት ጊዜ ኢራንን እንደጎበኙ የሚያሳይ የሳተላይት ምስሎችን ያወጣ ሲሆን፥ ይህም ጉብኝት ሩሲያ ለየክሬን ዘመቻዋ የሚሆን የድሮን ምርት ከቴሂራን ማግኘትን ዓላማ ያደረገ መሆኑን ጠቁሟል።
በዛሬው ጉባዔ ላይ ከሚገኙት ሀገራት መካከል አንዳቸውም ከአሜሪካ ጋር በሩሲያ ላይ ማዕቀብ ወይም ገደብ ለመጣል አልተንቀሳቀሱም።
የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ለሩሲያ ቢሊየነሮች እና በብዙ ሚሊየን ዶላር የሚገመት ጀልባዎቻቸው መዳረሻ ሆናለች።
ግብፅ በበኩሏ ለሩሲያ ቱሪስቶች በሯን ክፍት እንዳደረገች ነው።
ምንጭ፦ ዋሺንግተን ፖስት
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!