ስፓርት

በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ በለተሰንበት ግደይ የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች

By Mekoya Hailemariam

July 16, 2022

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በ18ኛው የኦሬገን የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ በሴቶች 10 ሺህ ሜትር በለተሰንበት ግደይ የመጀመሪያ የወርቅ ሜዳሊያ አግኝታለች።

በውድድሩ ኬንያውያን አትሌቶች ሁለተኛ እና ሶስተኛ በመሆን አጠናቀዋል።

እጅጋየሁ ታየ ስድስተኛ እና ቦስና ሙላቴ ስምንተኛ በመሆን ውድድሩን አጠናቀዋል።