አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 2 ፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) በትምህርት ሚኒስቴር የአጠቃላይ ትምህርት አዋጅ ረቂቅ ሰነድ ላይ በአዳማ ከተማ ውይይት እየተደረገ ነው።
የውይይት መድረኩ በትምህርት ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ የተከፈተ ሲሆን በቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይ ከተሳታፊዎችና ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት እየተደረገበት ይገኛል።
በመድረኩ የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮችና ባለሙያዎች፣ የክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሃላፊዎችና ባለሙያዎች፣ የመምህራን ትምህርት ኮሌጅ ሃላፊወችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት መገኘታቸውን ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
በቀጣይም ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ተጨማሪ የውይይት መድረክ እንደሚደረግ ታውቋል።
ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ! https://t.me/fanatelevision