አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 17፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ግብፅ ካይሮ ገብተዋል፡፡
የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማሪያ ዛካሮቫ እንዳስታወቁት ፥ ላቭሮቭ በካይሮ ቆይታቸው ከግብፅ ባለስልጣናት ጋር ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ላቭሮቭ የአፍሪካ ጉብኝታቸውን በይፋ የጀመሩ ሲሆን ፥ በቀጣይም በኢትዮጵያ፣ በኡጋንዳ እና በዲሞከራቲክ ኮንጎ የስራ ጉብኝት እንደሚያከናውኑ ሲጂቲኤን አፍሪካ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!