ስፓርት

በ18ኛው የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የ5000 ሜትር የወንዶች ፍጻሜ ውድድር ዛሬ ሌሊት ይደረጋል

By Meseret Awoke

July 24, 2022

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 17፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) በ18ኛው የኦሪገን የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የ5000 ሜትር የወንዶች ፍጻሜ ውድድር ዛሬ ሌሊት ይደረጋል።

ለሊት 10:05 በሚደረገው የወንዶች 5000 ሜትር ፍጻሜ ውድድር ላይ ሶስት ኢትዮጵያውን አትሌቶች የሚሳተፉ ሲሆን፥ ሙክታር ኢድሪስ፣ ሰለሞን ባረጋ እና ዮሚፍ ቀጀልቻ የሚሳተፉ ይሆናል።

በተመሳሳይ ለሊት 10:35 የሴቶች 800 ሜትር የፍጻሜ ውድድር ሲደረግ ድርቤ ወልተጂ በርቀቱ ኢትዮጵያን የምትወክል ብቸኛ አትሌት ናት።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!