ዓለምአቀፋዊ ዜና

የቻይና አፍሪካ ወጣቶች የቪዲዮ ፈጠራ ውድድር በቀጥታ ስርጭት መካሄድ ጀመረ

By Mikias Ayele

July 25, 2022

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቻይና የመገናኛ ብዙሃን ቡድን የቻይና አፍሪካ የወጣቶች ቪዲዮ ፈጠራ ውድድር ዛሬ በቀጥታ ስርጭት በይፋ ተጀመሯል።

ውድድሩ በቻይና የመገናኛ ብዙሃን ቡድን እና በዜጂያንግ ዩኒቨርሲቲ የሚዲያ እና ዓለም አቀፍ ባህል ኮሌጅ በጋራ የተዘጋጀ ነው።

ውድድሩ በቻይና እና በአፍሪካ ወጣቶች መካከል የመተሳሰብ ድልድይ ለመገንባት፣ የባህል ልውውጦችን ለማስተዋወቅ፣ የጋራ መግባባትን ለመፍጠር እና ወደፊት በሁለቱ ህዝቦች መካከል ዘላቂ የሆነ ወዳጅነት ለመፍጠር አጫጭር የቪዲዮ ፈጠራዎችን ለመጠቀም ያለመ ነው ተብሏል።

እ.ኤ.አ. በ2022 የተካሄደው የአፍሪካ ወጣቶች ጥናት እንደሚያመለክተው፥ አብዛኛው አፍሪካዊ ወጣት ቻይና በአፍሪካ ላይ አዎንታዊ ተጽእኖ ያሳደረች ሀገር ሆናለች ብሎ እንደሚያምን ያሳያል ተብሏል፡፡

የቻይና አፍሪካ የወጣቶች ቪዲዮ ውድድር መጀመር በሁለቱ ህዝቦች መካከል አጭር የቪዲዮ ፈጠራ መስክ እንዲዳብርና ወጣቶች አቅማቸውን እንዲገልጹ ያበረታታልም ነው የተባለው፡፡

ውድድሩ ከሐምሌ እስከ መስከረም ድረስ የሚካሄድ ሲሆን ባለሙያዎች አንደኛ፣ ሁለተኛ እና ሦስተኛ የወጡና የላቀ ስራ የሰሩ ተወዳዳሪዎችን ለሽልማት እንደሚያበቁ ተጠቁሟል።

አሸናፊ ቪዲዮዎች በአፍሪካ ውስጥ በቻይና የመገናኛ ብዙሃን ቡድን እና በዋና ዋና የመገናኛ ብዙሃን ላይ የመታየት እድል እንደሚኖራቸውም ሲጂቲኤን በዘገባው ጠቁሟል።