የሀገር ውስጥ ዜና

አቶ  ሙስጠፌ በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ድል ላስመዘገቡ አትሌቶች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉ

By Mikias Ayele

July 28, 2022

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳደር  አቶ ሙስጠፌ መሀመድ በ18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ድል ላስመዘገቡ አትሌቶች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳደሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት÷ ጀግኖች አትሌቶቻችን እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳደሩ በተለይም የአትሌቲክስ ቡድኑን ሙያዊ  እና ብቃት ባለው ሁኔታ በመምራት አመረቂ ውጤት ላስመዘገበችው ለፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት ኮሎኔል ደራርቱ ቱሉ የላቀ ምስጋና አቅርበዋል፡፡