አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢኮኖሚ ግንባታ ትልቅ ሚና ያላቸውን የቴክኒክና ሙያ ተቋማት በአረንጓዴ ልማት ማጀብ እና ሥራዎቻቸውን አቀናጅቶ ሙያውን መቃኘት አስፈላጊ ነው ሲሉ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገለጹ፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴርና የተጠሪ ተቋማት አመራሮችና ሠራተኞች የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር የችግኝ ተከላ አካሂደዋል።
በተለያዩ ቴክኒክና ሙያ ተቋማት ግቢ የተካሄደውን የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ባስጀመሩበት ወቅት የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ባደረጉት ንግግር÷ በኢኮኖሚ ግንባታ ትልቅ ሚና ያላቸውን የቴክኒክና ሙያ ተቋማት በአረንጓዴ ልማት ማጀብ እና ሥራዎቻቸውን አቀናጅቶ ሙያውን መቃኘት አስፈላጊ ነው ብለዋል።
ተቋማቱ ሀብት እና ሰፊ ቦታ ስላላቸው ሥራዎቻቸውን በአረንጓዴ ልማት ማጀብ ለኢኮኖሚ ግንባታ ያላቸውን ሚና የላቀ እንደሚያደርገው ገልጸዋል፡፡
በአራት ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች ከ2 ሺህ 500 በላይ ችግኞች የተተከሉ ሲሆን÷ ከ3 ነጥብ 3 ሚሊየን በላይ ችግኞችም በተለያዩ ኮሌጆች እንደሚተከሉ ሚኒስትሯ አመላክተዋል፡፡
በኢትዮ ቻይና ቴክኒክና ሙያ ኢንስቲትዩት፣ በጀኔራል ዊንጌት፣ በእንጦጦ፣ በምስራቅ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጆች የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ተከናውኗል፡፡
በታምሩ ከፈለኝ
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!