የሀገር ውስጥ ዜና

1ሺህ 159 ኢትዮጵያውያን ከሳኡዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

By Meseret Awoke

July 29, 2022

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ በሦስት ዙር በተከናወነ ዜጎችን ከሳኡዲ አረቢያ የመመለስ ስራ 1ሺህ 159 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ፡፡

ወደሀገራቸው ከተመለሱ ዜጎች መካከል 1 ሺህ 156 ወንዶች እና ሦስት እድሜያቸው ከ18 በታች የሆኑ ታዳጊዎች መሆናቸው ታውቋል፡፡

ለተመላሽ ዜጎችም ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ወደ ተዘጋጀላቸው የማቆያ ማእከላት እንዲሄዱ መደረጉን ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

እስካሁን በተከናወነው ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ስራ ቁጥራቸው 58 ሺህ 301 ኢትዮጵያውያንን ከሳዑዲ አረቢያ መመለስ ተችሏል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!