የሀገር ውስጥ ዜና

አቶ ሽመልስ አብዲሳ አሶሳ ከተማ ገቡ

By Shambel Mihret

July 31, 2022

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ የተመራ የክልሉ ከፍተኛ ልዑክ አሶሳ ከተማ ገባ።

ልዑኩ አሶሳ ህዳሴ አየር ማረፊያ ሲደርስ በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን እና በከፍተኛ አመራሮች አቀባበል ተደርጎለታል።

ልዑኩ በክልሉ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ላይ ሚሳተፍ እና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ሚዲያ ምርቃት ላይ የሚታደም መሆኑን ከክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!