የሀገር ውስጥ ዜና

በታንዛንያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 60 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

By Melaku Gedif

August 01, 2022

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በታንዛንያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 60 ኢትዮጵያውያን በፈቃዳቸው በዛሬው ዕለት ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።

በታንዛንያ የዓለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት ፕሮግራም ሃላፊ ዴቪድ ሆፍሜየር በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ ዜጎቹ በዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት፣ በታንዛንያ የኢትዮጵያ ኤምባሲና የታንዛንያ የስደተኞች ጉዳይ ጽሕፈት ቤት ባደረጉት ትብብር ነው ወደ ሀገራቸው የተመለሱት፡፡

ሃላፊው ኢትዮጵያውያኑ በአራተኛ ዙር ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ የስዊድን መንግሥት ላደረገው የገንዘብ ድጋፍ እና ድርጅቶቹ ላደረጉት ትብብት ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ዜጎች በቀጣይ በተቀመጠላቸው የጉዞ መርሐ ግብር መሠረት ወደ ኢትዮጵያ መመለስ እንዲችሉ አስፈላጊ የሆኑ ቅድመ ሁኔታዎች በመሟላት ላይ እንደሚገኙም ተጠቁሟል፡፡