የሀገር ውስጥ ዜና

በነሐሴ የተጠናከረ ዝናብ ስለሚኖር ጎርፍና የመሬት መንሸራተት ሊከሰት ይችላል- ብሔራዊ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት

By Feven Bishaw

August 01, 2022

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በነሐሴ የሚኖረውን የተጠናከረና ተከታታይነት ያለው ከባድ ዝናብ ተከትሎ በአንዳንድ አካባቢዎች ላይ ጎርፍና የወንዞች ሙላት እንዲሁም የመሬት መንሸራተት ሊኖር እንደሚችል የብሔራዊ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አሳሰበ፡፡

በመሆኑም በየአካባቢው ህብረተሰቡና የሚመለከታቸው አካላት ከወዲሁ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ኢንስቲትዩቱ መክሯል፡፡