የሀገር ውስጥ ዜና

1 ሺህ 33 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

By Melaku Gedif

August 01, 2022

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 1 ሺህ 33 ኢትዮጵያውያን በዛሬው ዕለት ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡

ከተመላሾቹ ውስጥ 1 ሺህ 24 ወንዶች፣ 2 ሴቶች ፣ 7 ህፃናት እና እድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች እንደሚገኙበት ተገልጿል፡፡

ለተመላሽ ዜጎች ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ወደተዘጋጀላቸው የማቆያ ማዕከላት እንዲሄዱ መደረጉንም ከሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡