የሀገር ውስጥ ዜና

ዳያስፖራው በሀገሪቱ ዘላቂ ጥቅም ላይ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እንዲንቀሳቀስ እየሰራን ነው – የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት

By Feven Bishaw

August 01, 2022

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የዳያስፖራው ማህበረሰብ በሀገሪቱ ዘላቂ ጥቅም ላይ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ የበለጠ እንዲንቀሳቀስ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት አስታወቀ፡፡

ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፓሬት ጋር ቆይታ ያደረጉት የአገልግሎቱ ምክትል ዳይሬክተር ዶክተር መሀመድ ኢድሪስ÷ ኢትዮጵያ ከሌሎች ሀገራት ጋር ያላትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቶች ለማጠናከር እና ራሷን ለማስተዋወቅ ዳያስፖራዉ የሀገሩ አምባሳደር እንደመሆኑ ጠንካራ ስራዎች እንደሚሰራ ይጠበቃል ብለዋል፡፡