የሀገር ውስጥ ዜና

ሌተናል ጀኔራል ብርሃኑ በቀለ ከሶማሊላንድ ፕሬዚዳንት እና ወታደራዊ አመራሮች ጋር ተወያዩ

By Melaku Gedif

August 03, 2022

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሌተናል ጀኔራል ብርሃኑ በቀለ የመከላከያ ሚኒስቴርን በመወከል በቀጠናው ፀጥታና ደኅንነት ጉዳይ ላይ ከሶማሊላንድ ፕሬዚዳንት እና ወታደራዊ አመራሮች ጋር ተወያዩ፡፡

ጄኔራሉ መኮንኑ ሶማሊላንድ ሃርጌሳ ኢጋል ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ÷ የሶማሊላንድ ወታደራዊ አመራሮች አቀባባል አድርገውላቸዋል።

ሌተናል ጀኔራል ብርሃኑ በኢትዮጵያና ሶማሊላንድ እንዲሁም በቀጠናው ሊኖር ስለሚገባው የጋራ የፀጥታና ደኅንነት ጉዳዮች ላይ ስለሚኖር ትብብር ተወያይተዋል።

ውይይቱ ከሶማሊላንድ ፕሬዚዳንት፣ ወታደራዊ አመራሮች እና ከብሔራዊ ደኅንነት የስራ ሃላፊዎች ጋር የተካሄደ መሆኑን የመከላከያ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡