ስፓርት

በሻምፒዮናው የማጣሪያ ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ለፍፃሜ ውድድር አለፉ

By Amare Asrat

August 03, 2022

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 27 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኮሎምቢያ ካሊ እየተካሄደ ባለው 19ኛው የዓለም ከ20 ዓመት በታች የአትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ዛሬ በተካሄዱ የማጣሪያ ውድድሮች ለፍፃሜ ውድድር አልፈዋል።

በ3 ሺህ ሜትር የወንዶች የማጣሪያ ውድድር አትሌት ድሪባ ግርማ እና አትሌት መልኬነ አዝዝ ከየምድባቸው 3ኛ በመውጣት ወደ ፍፃሜ አልፈዋል።

በ3 ሺህ ሜትር መሰናክል የወንዶች የማጣሪያ ውድድር አትሌት ሣሙኤል ፍሬው እና አትሌት ሳሙኤል ዱጉና ከምድባቸው 1ኛ በመውጣት ለፍፃሜው ውድድር ማለፋቸውን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መረጃ ያመላክታል።