አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀገር መከላከያ ኃይል ስምሪት ኃላፊና ጊዜያዊ የፀጥታ ኮማንድ ፖስት አስተባባሪ ሜ/ጄኔራል ተስፋዬ አያሌው ከደቡብ ምዕራብ ሶማሊያ መስተዳድርና የፀጥታ አካላት ጋር ስለቀጠናው ሰላምና የፀጥታ ሁኔታ ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸው÷ በተለይም አልሸባብን ለመደምሰስ በሚካሄደው ዘመቻ በቅንጅት ለመሥራት መክረዋል፡፡
በሜ/ጄኔራል ተስፋዬ አያሌው የተመራ ከፍተኛ የሠራዊቱ አመራሮችና የፀጥታ አካላት ልዑክ ባይደዋ ሲደርስ÷ በሴክተር ሦስት ዋና አዛዥ ብ/ጄ ዘውዱ ሰጥአርጌ እና በሴክተሩ ከፍተኛ መኮነኖች አቀባበል ተደርጎለታል።
ስለቀጠናው የሰላምና የፀጥታ ሁኔታ እንዲሁም አጠቃላይ የአልሸባብ እንቅስቃሴ ምን እንደሚመስል በሴክተሩ ዋና አዛዥ ገለፃ መደረጉን የመከላከያ ሠራዊት መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!