የሀገር ውስጥ ዜና

የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል እና “ግሎባል ዴቨሎፕመንት” በትምርቱ ዘርፍ የኢንቨስትመንት ስምምነት ተፈራረሙ

By ዮሐንስ ደርበው

August 05, 2022

 

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግሥት ከግሎባል ዴቨሎፕመንት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ጋር በትምርቱ ዘርፍ በክልሉ ለሚደረግ ኢንቨስትመንት ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

ስምምነቱን የተፈራረሙት÷ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻደሊ ሀሰን እና የግሎባል ደቨሎፕመንት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ፕሬዚዳንት ዶክተር ማቲዎስ ግችሌ ናቸው፡፡

አቶ አሻደሊ ሀሰን በስምምነቱ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ ክልሉ በተለይ በትምህርቱ ዘርፍ የሚፈለገውን ዕድገት ያላመጣ እና የበለጠ ሊሠራበት እንደሚገባ ጠቁመው÷ ስምምነቱ ወደፊት የተማረ ትውልድ በማፍራት ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽዖ እንደሚያበረክት ያላቸውን እምነት ገልፀዋል፡፡

ግሎባል ደቨሎፕመንት ያለውን ልምድ እና እውቅና ተጠቅሞ  በተለያዩ ዘርፎች ያሉ የኢንቨስትመንት አማራጮችን በማስተዋወቅ ረገድ የበኩሉን እንዲወጣና ከክልሉ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ተባብሮ እንዲሠራ መጠየቃቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ አመላክቷል፡፡